Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአማራ ክልል የክረምት የአደባባይ በዓላት የማጠቃለያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ጳጉሜን 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአማራ ክልል የክረምት የአደባባይ በዓላት የማጠቃለያ መርሀ ግብር በባሕር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።

መርሐ ግብሩ “ባህላዊ እሴቶቻችን የፈተና መሻገሪያ፥ የጋራ ተስፋችን መገንቢያ” በሚል መሪ ሀሳብ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በዓላቱ ሻደይ፣ አሸንድዬ፣ ሶለል፣ ቡሔ፣ ከሴ አጨዳ፣ እንግጫ ነቀላ እና አሱሪቴ ሲሆኑ፤ ከነሐሴ ወር አጋማሽ ጀምሮ እስከ አዲስ ዓመት መግቢያ ድረስ የሚከበሩ በዓላት ናቸው።

በማጠቃለያ መርሐ ግብሩ ላይ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ ከተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች የመጡ የባህል አምባሳደሮችና የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ተገኝተዋል፡፡

በደሳለኝ ቢራራ

Exit mobile version