Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በክልሉ የኢትዮጵያን የማንሰራራት ጉዞ ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋገሩ ስኬቶች ተመዝግበዋል – አቶ ጥላሁን ከበደ

አዲስ አበባ፣ጳጉሜን 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በተገባደደው ዓመት የኢትዮጵያን የማንሰራራት ጉዞ ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋገሩ በርካታ ስኬቶች ተመዝግበዋል አሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ፡፡
የክልሉ መንግሥት በ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም፣ በ2019 መሪ ዕቅድና የቀጣይ አምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ የሚመክር መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በተገባደደው ዓመት ያጋጠሙ ተደራራቢ ችግሮችን ወደ ዕድል በመቀየር ክልሉን ከተስፋ ብርሃን ወደሚጨበጥ ዕድገት ማሸጋገር ተችሏል።
በ2019 በጀት ዓመት የሕዝብ ጥያቄዎችን በዘላቂነት ለመመለስ የሚያስችሉ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አመልክተዋል፡፡
በዛሬው ዕለት እየተከበረ የሚገኘው የማንሰራራት ቀን በዓመቱ የታዩ ጥንካሬዎችን የምናስቀጥለበትና ክፈተቶችን በመለየት ክልሉን የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ የጀመርነውን ጉዞ ለማሳለጥ የሚያግዝ ነው ብለዋል፡፡
በየደረጃው ያለው አመራር ከህዝብ የተቀበለውን አደራና ኃላፊነቱን በአግባቡ በመወጣት ለሁለንተናዊ ብልፅግና እንዲተጋ አሳስበዋል፡፡
በኢብራሂም ባዲ
Exit mobile version