አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የማንሠራራት ቀንን ምክንያት በማድረግ በተለያዩ ዘርፎች የተከወኑ ተግባራትን የሚያሳይ ዐውደ-ርዕይ ተከፍቷል።
የከተማዋ የመብራት አገልግሎት ባለስልጣን ያዘጋጀው ዐውደ-ርዕይ ተቋሙ ባለፉት ሁለት ዓመታት የሰራቸውን በቴክኖሎጂ የተደገፈ ዘመናዊ የመብራት መሰረተ ልማት የሚያሳይ ነው።
በዐውደ-ርዕዩ ከ41 ሺ በላይ ዘመናዊ የመብራት መሰረተ ልማትን በጂአይኤስ በማደራጀት ከአንድ ማዕከል መቆጣጠርና ማስተዳደር መቻሉ ተመላክቷል።
በተመሳሳይ የከተማዋ መንገዶች ባለሥልጣን ያዘጋጀውና ባለፉት አምስት ዓመታት በከተማዋ የመንገድ ዘርፍ የተከናወኑ ትልልቅ እመርታዎችንና ተያያዥ የልማት ሥራዎችን የሚያሳይ ዐውደ-ርዕይም ተከፍቷል።
በዐውደ-ርዕዩ የከተማዋን ነዋሪዎች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ የሚያቀልሉ እና የትራፊክ ፍሰቱን ማሻሻል የቻሉ አዳዲስ የመንገድ መሠረተ ልማቶች በፎቶ መቅረባቸውን የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል።

