Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በታሪክ ቅብብሎሽ የተረከብናትን ሀገር በማጽናት ለትውልድ እናስረክባለን – የመከላከያ ሠራዊት አባላት

አዲስ አበባ፣ጳጉሜን 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በታሪክ ቅብብሎሽ የተረከብናትን ሀገር በመጠበቅና በማጽናት ለመጪው ትውልድ እናስረክባለን አሉ የመከላከያ ሠራዊት የምስራቅ ዕዝ አባላት።

የምስራቅ ዕዝ ሠራዊት አባል የሆኑት ሌተናል ኮሎኔል ፈይሳ በዳዳ ፥ ቀደምት አባቶቻችን በውጪ ወራሪና በውስጥ ባንዳ ሳይበገሩ በከፈሉት መስዋዕትነት ዳር ድንበሯና የህዝቧ አንድነት የተከበረባት ሀገርን አስረክበውናል ብለዋል።

ይህ አይበገሬነት የጽናት ተምሳሌት ነው ብለው የመከላከያ ሠራዊት አሁን ላይ የሀገሩን ዳር ድንበር የማስከበር ሀላፊነቱን በጽናት እየተወጣ መሆኑንም አመልክተዋል።

በውስጥ ጠላት ሳንበገር በታሪክ ቅብብሎሽ የተረከብናትን ሀገር በመጠበቅና በማጽናት ለመጪው ትውልድ እናስተላልፋለን ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በኢትዮጵያ የጽናት ቀን መከበሩም በተለይ ለመከላከያ ሠራዊት ትልቅ ትርጉም ያለው መሆኑንም አንስተዋል።

ዛሬ ጳጉሜን 3 “የጽናት ቀን” በሚል ስያሜ የጸጥታና ደህንነት ተቋማት ኢትዮጵያን በጽናት ለማስቀጠል ያበረከቱትን የላቀ አስተዋጽኦ በመዘከር በሃገር ደረጃ እየተከበረ ይገኛል።

Exit mobile version