Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በሀገር አቀፍና በክልል ደረጃ የተመዘገቡ አኩሪና ታሪካዊ ድሎች የጽናት ማሳያ ናቸው – አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሀገር አቀፍና በክልል ደረጃ የተመዘገቡ አኩሪና ታሪካዊ ድሎች የጽናት ማሳያ ናቸው አሉ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ፡፡
ጳጉሜን-3 የጽናት ቀን በሀረሪ ክልል በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የጽናት ቀንን ስናከብር የሀገር ሰላምና ዳር ድንበር ለመጠበቅ መስዋዕትነት የከፈሉና እየከፈሉ ለሚገኙ የሀገር መከላከያ፣ የፌዴራልና የክልል ፖሊስ አባላት ተገቢውን ክብር በመስጠት ሊሆን ይገባል።
ጽናት ኢትዮጵያውያን የህልውናና የሉዓላዊነት እሴቶቻቸውን ለማስቀጠል የሚከፍሉት ዋጋ ነው ብለዋል፡፡
እኔ ከሚለው ጠባብ እሳቤ በመውጣት እኛ በሚለው ታላቅ ብሔራዊ የሀገር ግንባታ ርዕይ ጥላ ስራ መሰለፍ እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል፡፡
ዓመቱ ወደ ባህር በር ለመመለስ በሰላማዊና ዲፕሎማሲያዊ መንገድ ጉዞ የተጀመረበት መሆኑን ጠቁመው፤ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ እና ሀገራዊ የምክክር ጉባኤው በስኬት የተጠናቀቁበት ዓመት እንደነበር አንስተዋል፡፡
በተጨማሪም ሌሎች ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች የተጀመሩበት ዓመት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በክልሉም ሰላምን በማጠናከር ስኬታማ የኮሪደር ልማት፣ የግብርናና ሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶች ማከናወን የተቻለበት መሆኑን አብራርተዋል፡፡
እንዲሁም በቱሪዝም ዘርፉ በተከናወኑ በርካታ ስራዎች ተጨባጭ ውጤቶች የተመዘገቡበት እንደነበር ገልጸዋል፡፡
በተስፋዬ ኃይሉ
Exit mobile version