Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከንቲባ አዳነች አቤቤ አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ማዕድ አጋሩ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የ2019 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች ማዕድ አጋርተዋል፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ “በኅብር ቀን” ሀገር በቀል እሴቶችን በተግባር በመጠቀም አብሮነትን፣ መረዳዳትንና ሰው ተኮር ተግባራትን ባህል በማድረግ ማህበራዊ ትስስርን ለማጠናከር በሁሉም ወረዳዎች፣ ክፍለ ከተሞችና በማዕከል ለከተማዋ ነዋሪዎች ማዕድ አጋርተናል ብለዋል።

ጧሪ ደጋፊ ለሌላቸው፣ ለማህበራዊ ችግር ለተጋለጡ፣ ለአረጋውያን፣ ለአቅመ ደካሞች፣ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሠራተኞችን ጨምሮ ከለውጡ ዘመን ጀምረን እርስ በርስ በመረዳዳት ያለው ለሌለው እንዲያካፍል በማድረግ ማዕድ የማጋራት እሴትን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በዛሬው ዕለት በተካሄደው የማዕድ ማጋራት መርሐ ግብርም አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ፍቅራችንን፣ አብሮነታችንን እና አክብሮታችንን ለከተማችን ነዋሪዎች አጋርተናል ነው ያሉት፡፡

ከንቲባ አዳነች አዲሱ ዓመት የፍቅር፣ የሰላም፣ በትጋት ሰርተን የምንለወጥበት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

መስጠት አያጎድልም በሚል መርሕ ካላቸው በማካፈል በከተማዋ በሚደረጉ የማዕድ ማጋራት ሥራዎች ውስጥ አስተዋፅኦ ያደረጉ አካላትን በሙሉ አመስግነዋል።

Exit mobile version