Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያ የበለጸገ የህብረተሰብ ሀብት ክምችት ያላት ሀገር ናት – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የበለጸገ የህብረተሰብ ሀብት ክምችት ያላት ሀገር ናት አሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፡፡
በኅብር ቀን አሮጌውን ዓመት አልፈን ወደ አዲስ ዓመት መሸጋገርን ከሚያበስሩ ውብ እና ህብራዊ ባህሎቻችን መካከል የሆኑትን የአበባአየሽ ወይ፣ የአሸንዳ፣ ጎቤ፣ ሽኖዬ፣ ሻደይ ጭፈራዎች በዓድዋ ድል መታሰቢያ ተከብረዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ ኢትዮጵያ የበለጸገ የህብረተሰብ ሀብት ክምችት ያላት ሀገር ናት ብለዋል፡፡
የመደመር መንግሥትም እነዚህን ሀብቶች በመጠበቅ፣ በመንከባከብና በማልማት ለሀገር እድገትና ለህብረተሰብ ልማት ማዋል ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ውብ ኢትዮጵያዊ ባህሎቻችን ጎልተው እንዲወጡ፣ ከባህሉና እሴቱ ማግኘት የሚገባንን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጥቅም እንዲያስገኙ እና የቱሪዝም መስህብ እንዲሆኑ እየሰራን ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡
Exit mobile version