አዲስ አበባ፣ጳጉሜን 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ለ 2ሺህ 735 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ አድርጓል፡፡
የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ቢሮ ኃላፊ ጉዮ ዋርዮ በሰጡት መግለጫ ይቅርታ የተደረገላቸው ታራሚዎች በማረሚያ ቤት ቆይታቸው መልካም ስነምግባር ያላቸውና ጸባያቸው የታነጸ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በይቅርታ የተፈቱ ታራሚዎቹ 2ሺህ 518 ወንዶች እና 217 ሴቶች መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡
ሕጋዊ አሠራርን መሰረት በማድረግ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ለታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉንም አስረድተዋል፡፡
ይህም የማህበረሰቡን ሰላምና ጸጥታ ለማጽናት እንደሚያስችል ጠቁመው፤ ከእድሜ ልክ እስከ 12 አመት እና ከዚያ በላይ ፍርደኞች በዚህ ይቅርታ ተጠቃሚ መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡
የሞት ፍርድ የተወሰነባቸው እና ከተፈቱ በኋላ ድጋሚ ወንጀል የፈጸሙ በዚህ ይቅርታ ተጠቃሚ እንደማይሆኑ አስገንዝበዋል፡፡

