አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አዋሽ ባንክ መጪውን የ2019 አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ የ2 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር የአበባየሆሽ / ሽኖዬ የቲክቶክ ቻሌንጅ ሽልማት ማዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡
ተወዳዳሪዎች በአበባየሆሽ ወይም ሽኖዬ ግጥም በማዘጋጀትና የፈጠራ ጥበብን በማሳየት እስከ 1 ሚሊየን ብር መሸለም ይችላሉ፡፡
ስለሆነም ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥን በአማርኛ ወይም በአፋን ኦሮሞ ግጥም በማዘጋጀት በአበባየሆሽ ወይም ሽኖዬ ዜማ ፈጠራ የታከለበት የቲክቶክ ቪዲዮ መስራት ይጠበቅባቸዋል፡፡
የተሰራውን ቪዲዮም ከጳጉሜን 3 አስከ መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም ቲክቶክ ገጻቸው ላይ በመለጠፍ መወዳደር፣ ማሸነፍና መሸለም ይችላሉ ፡፡
ርዕሰ ጉዳዮች፡-
1. የአዋሽ ባንክን አጠቃላይ ገጽታን በተመለከተ
2. የአዋሽብር ፕሮ የዲጂታል አገልግሎት እና
3. የአዋሽ ሬሚት የዲጂታል አገልግሎት።
ተወዳዳሪዎች የመወዳደሪያ ዜማ የግጥም ይዘት ከተዘረዘሩት አንዱን በመምረጥ መወዳደር ይችላሉ።
አዋሽ ባንክ ለውድድሩ ያዘጋጀው ሽልማት፡-
1ኛ. 1 ሚሊየን ብር
2ኛ. 700 ሺህ ብር
3ኛ. 500 ሺህ ብር
ተወዳዳሪዎች የሰሩትን የቪዲዮ ማስፈንጠሪያ በዚህ ቴሌግራም https://t.me/+ma2_m3DGlTsxZDc0 መላክ ይጠበቅባቸዋል።
ተወዳዳሪዎች ለውድድር ብቁ ለመሆን ቢያንስ 500 ሺህ ቪው እና 10 ሺህ ላይክ ማግኘት አለባቸው።
ለበለጠ መረጃ እና የመወዳደሪያውን ደንብና ሁኔታዎች ለማግኘት ማስፈንጠሪያውን https://t.me/awash_bank_official/7666 ይጫኑ!
ተወዳዳሪዎች የአዋሽ ባንክን የቲክቶክ ገጽ መጥቀስ https://www.tiktok.com/@awashbank_tiktok አለባቸው።

