Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

2018 ዓመት በክልላችን የህዝብ ተጠቃሚነት የተረጋገጠበት ዓመት ነው – ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 2018 ዓመት በክልላችን የህዝብ ንቁ ተሳትፎና ተጠቃሚነት የተረጋገጠበት ዓመት ነው አሉ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ፡፡
በሀረሪ ክልል ጳጉሜን 5 “የነገ ቀን” በድምቀት ተከብሯል።
በዚሁ ወቅት አቶ አርዲን በድሪ ፥ የአዲስ ዓመት መባቻ ያለፈውን ገምግመን፣ አዲሱን በላቀ የተስፋ እና የስራ መንፈስ የምንቀበልበት ነው ብለዋል።
የ2018 ዓመት በሁሉም ዘርፎች አበረታች ውጤቶች የተመዘገቡበት ልዩና ታሪካዊ ዓመት ነበር ሲሉም ተናግረዋል።
በተለይ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫና ሃገራዊ ምክክር ብሎም በርካታ የልማት ስራዎች በስፋት በስኬት የተከወኑበት መሆኑ 2018 ዓመትን የተለየ ስኬታማ ዓመት ያደርገዋል ነው ያሉት።
2019 ዓመት ለወደፊቷ ኢትዮጵያ ጠንካራ መሠረት የምንጥልበት ዓመት ይሆናል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ለፋና ዲጂታል የላከው መረጃ ያመላክታል።
Exit mobile version