Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ለአዲሱ ዓመት ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡-

👉ዘመን ከፈጣሪ ለሰው የተሰጠ መሥሪያ መጽሐፍ ሲሆን፣ ለእያንዳንዱ ሰው የተሰጡ የተወሰኑ ገጾች አሉት። የመጨረሻው ገጽ እስኪከደን ድረስ የፈለግነውን የመጻፍ መብት በእጃችን ይገኛል።

👉የትናንቱ ዘመን ጠባሳውንም ዐሻራውንም፣ ዕዳውን ምንዳውንም ሰጥቶን አልፏል። አሁን ወሳኙ ነገር በቀሩን ዘመናት ምን ቁም ነገር እንሰራለን? የሚለው ነው።

👉ኢትዮጵያውያን ዛሬ ለትውልድ የሚተርፍ አስደናቂ ታሪኮችን እየሰራን ነው።

👉እነሆ የዘመን መጽሐፋችንን የ2019 አዲስ ምዕራፍ የምንጀምረው ሀገራዊ ምክራችንን በስኬት አጠናቅቀን ነው።

👉ኢትዮጵያውያን ሊመካከሩ አይችሉም፤ ቢመካከሩን ወደ ተቀራቢ ሐሳብ አይደርሱም የሚለውን ሟርት አክሽፈነዋል።

👉ከፀሐይ በታች ባሉ ጉዳዮች የመወያየት፣ የመነጋገርና የመግባባት ፖቲካዊ ባህልን ማዳበራችን ታላቅ ስኬት ነው።

👉በተካሄደው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ሕዝባችንን ዋና ባለቤትና ዋና ተዋናይ በማድረግ ተጠናቅቋል።

👉ወደ ሀገራዊ ምክክር የመጡ ልዩ ልዩ ወገኖች በአንድም በሌላም ስሕተት የታሠሩ ወገኖች በይቅርታ እና በህግ አግባብ እንዲፈቱ ጠይቀው ነበር። መንግሥት ይሄንን ተቀብሎ በሂደቱ የተስማሙትን ፈትቷል።

👉በዚህ የይቅርታ ሂደት የተፈቱ ወገኖች በሀገራዊ ምክክር ምክረ ሐሳቦች ላይ አዎንታዊ ሚና ይጫወታሉ ተብሎ ይታመናል።
መነጋገር፣ መከራከርና መፎካከር ሲቻል ግጭትና ጦርነት አዋጪ አይደለም። የብዕርና የሐሳብ ጊዜ እንጂ የጠመንጃ እና የጉልበት ጊዜ አልፏል።

👉የኢትዮጵያ የዘመን መጽሐፍ ካሁን በኋላ የጠመንጃና የጉልበት ታሪክን አይመዘግብም።

👉አዲሱ ዓመት በኢትዮጵያ የዘመን መጽሐፍ ላይ አዲስ ታሪክ፣ አዲስ ሐሳብና አዲስ ሥልጣኔ የምንጽፍበት እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ።

Exit mobile version