አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2018 ዓ.ም (ኤፍ ኤም ሲ) የ2018 ዓ.ም የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር 8 ነጥብ 2 ቢሊየን ችግኞችን በመትከል በስኬት ተጠናቅቋል አሉ የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ፡፡
አቶ አዲሱ አረጋ የመርሐ ግብሩን መጠናቀቅ አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት፥ የ2018 የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር 8 ቢሊየን ቸግኞችን እንደ ሀገር ለመትከል ታቅዶ በከፍተኛ ትጋት ሲሰራበት ቆይቷል።
በዚህም እስከ ጳጉሜን 5 ቀን 2018 ድረስ በተከናወነው የቸግኝ ተከላ መርሃ ግብር 8 ነጥብ 2 ቢሊየን ችግኞች በመትከል ከእቅድ በላይ በሆነ አፈጻጸም በስኬት ተጠናቅቋል ብለዋል፡፡
ባለፉት 8 ዓመታት በአጠቃላይ 50 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ እየተሰራ እንደነበር ጠቁመው እስከዛሬዋ ቀን ድረስ የዘንድሮውን መርሃ ግብር ጨምሮ 56 ነጥብ 8 ቢሊየን ችግኝ መተከሉን ተናግረዋል፡፡
ሚኒስትሩ በመርሃ ግብሩ ለተሳተፉ እና ለስኬቱ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላደረጉ መላው ኢትዮጵያውያን እና ተቋማት ምስጋናም አቅርበዋል፡፡
በአመለወርቅ ደምሰው

