Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአፍሪካ ኅብረት እና ኢጋድ ለኢትዮጵያ ህዝብና መንግሥት ለአዲሱ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 1፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ ኅብረት እና ኢጋድ ለኢትዮጵያ ህዝብና መንግሥት ለአዲሱ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ፣ የኢትዮጵያን አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ለኢትዮጵያ መንግሥት እና ሕዝብ የሰላም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
በአዲሱ ዓመት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሰላምን፣ አንድነትን እና ብልጽግናን የተመኙት ሊቀመንበሩ፣ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን የተባበረች፣ ሰላማዊ እና የበለጸገች አፍሪካን እውን ለማድረግ ከአጋር አካላት ጋር ተባብሮ ለመሥራት ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።
እንዲሁም ኢትዮጵያ ለአፍሪካ አንድነት፣ ነጻነት እና ለአህጉሪቱ የጋራ ዓላማዎች ያበረከተችውን ታሪካዊ አስተዋጽኦ አድንቀዋል።
በተመሳሳይ የምሥራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) ለኢትዮጵያ መንግሥት እና ህዘብ አዲሱ ዓመት የሰላም እና የፍቅር እንዲሆን ተመኝቷል፡፡
Exit mobile version