Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ 7 ጨዋታዎች ይደረጋሉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በአራተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት 7 ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡

በዚህም ምሽት 4 ሰዓት ላይ አርሰናል ከሜዳው ውጪ ተጉዞ ከሰንደርላንድ ጋር ጨዋታውን ያደርጋል፡፡

በሊጉ እስካሁን ድረስ ሁሉንም ጨዋታዎች ያሸነፈው አርሰናል ተከታታይ 4ኛ ድሉን ለማሳካት ወደ ሜዳ የሚገባ ይሆናል፡፡

ባለሜዳው ሰንደርላንድ በበኩሉ ወደ ድል ለመመለስ የሚያደርገው ፍልሚያ ይጠበቃል፡፡

ሁለቱ ቡድኖች በሁሉም ውድድር እርስበርስ ካደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች አርሰናል አራቱን በማሸነፍ የበላይነት አለው፡፡ በቀሪው አንድ ጨዋታ ደግሞ አቻ ተለያይተዋል፡፡

ከዚህ ጨዋታ አስቀድሞ አመሻሽ 11 ሰዓት ላይ ቼልሲ በሜዳው ስታምፎርድ ብሪጅ ሃል ሲቲን ያስተናግዳል፡፡

ከሁለት ተከታታይ ድል በኋላ በ3ኛ ሳምንት የሊጉ ጨዋታ ሽንፈት የገጠመው ቼልሲ ወደ ድል ለመመለስ ወደ ሜዳ ይገባል፡፡

እስካሁን በሊጉ ያልተሸነፈው ተጋጣሚው ሃል ሲቲ በበኩሉ ያለመሸነፍ ጉዞውን ለማጠናከር ይፋለማል፡፡

በተመሳሳይ አመሻሽ 11 ሰዓት ላይ ሊቨርፑል በሜዳው አንፊልድ ሮድ ፉልሃምን ያስተናግዳል፡፡

በ3ኛ ሳምንት የሊጉ ጨዋታ የመጀመሪያ ድሉን ያሳካው ሊቨርፑል ተከታታይ ድሉን ለማሳካት የሚያደርገው ፍልሚያ ይጠበቃል፡፡

ተጋጣሚው ፉልሃም በበኩሉ የውድድር ዓመቱን የመጀመሪያ ድል ለማሳካት ወደ ሜዳ ይገባል፡፡

ቦርንማውዝ ከብሬንትፎርድ፣ አስቶንቪላ ከኖቲንግሃም ፎረስት እንዲሁም ክሪስታል ፓላስ ከኢፕስዊች ታውን በተመሳሳይ አመሻሽ 11 ሰዓት ላይ የሚደረጉ ጨዋታዎች ናቸው፡፡

ምሽት 1 ሰዓት 30 ላይ ቶተንሃም ሆትስፐር ከኤቨርተን ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

Exit mobile version