Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያ በአፍሪካ የሩሲያ ቁልፍ አጋር ናት – ፕሬዚዳንት ፑቲን

አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉር የሩሲያ ቁልፍና አስተማማኝ አጋር ናት አሉ የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከ18ኛው የብሪክስ መሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን ተወያይተዋል።

ፕሬዚዳንት ፑቲን በዚሁ ወቅት፥ ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉር የሩሲያ የረጅም ጊዜ እና አስተማማኝ አጋር ናት ብለዋል።

ሩሲያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ከፍ አድርጋ እንደምትመለከተውና የሃገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት በእኩልነት እና በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ መሆኑን ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንት ፑቲን ኢትዮጵያ ከጥር 2024 ጀምሮ የብሪክስ ሙሉ አባል መሆኗን በማስታወስ ሀገሪቱ በብሪክስ ማዕቀፍ ውስጥ አዎንታዊ አስተዋጽኦ እያበረከተች መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

ፕሬዚዳንቱ ለኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ለ2019 አዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውንም አስተላልፈዋል።

ሁለቱ መሪዎች በኢትዮጵያ እና ሩሲያ መካከል ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል።

Exit mobile version