Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ቼልሲ እና ሊቨርፑል ነጥብ ጣሉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በ4ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ጨዋታ ቼልሲ እና ሊቨርፑል ከተጋጣሚዎቻቸው ጋር አቻ በመለያየት ነጥብ ጥለዋል።
በዚህ ዓመት ወደ ሊጉ የተቀላቀለቀውን ሃል ሲቲን በሜዳው ያስተናገደው የለንደኑ ክለብ ቸልሲ2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቷል፡፡
የቼልሲን ግቦች ሞርጋን ሮጀርስ እና ጇ ፔድሮ ግቦችን ሲያስቆሩ ቤሎሚ በ28ኛው እና በ34ኛውየሀል ሲቲን ሁለት ግቦች ያስቆጠረ ተጫዋች ነው።
እንዲሁም ሊቨርፑል ከፉልሃም ያደረገው ጨዋታ ምንም ግብ ሳይቆጠር በአቻ ውጤት ተጠናቋል።
ከዚህ በተጨማሪ በተመሳሳይ ሰዓት በተደረጉ ጨዋታዎች አስቶን ቪላ በኖቲንግሃም ፎረስት 2 ለ 1 እንዲሁም ክሪስል ፓላስ በኤፕስዊች ታውን 3 ለ 2 ሲሸነፉ በርንማውዝ ከብሬንትፎርድ 2 ለ 2 ተለያይተዋል፡፡
Exit mobile version