Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ተጠባቂው 199ኛው የማንቼስተር ደርቢ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 4ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሁለቱ የማንቼስተር ከተማ ክለቦች ማንቼስተር ዩናይትድና ማንቼስተር ሲቲ የሚያደርጉት ጨዋታ በጉጉት ይጠበቃል።

የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ምሽት 12፡30 በኦልድ ትራፎርድ የሚካሄድ ሲሆን÷ ክለቦቹ በሁሉም ውድድሮች ሲገናኙ ይህ ለ199ኛ ጊዜ ነው።

ማንቼስተር ሲቲ በኤንዞ ማሬስካ እየተመራ ባደረጋቸው ባለፉት ሦስት የሊጉ ጨዋታዎች ሦስቱንም በማሸነፍ ነው የምሽቱን መርሐ ግብር የሚያከናውነው።

ቀያዮቹ ሰይጣኖች በበኩላቸው በሊጉ ባደረጓቸው ባለፉት ሦስት ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻሉት አንዱን ብቻ ሲሆን÷ ማግኘት ከነበረባቸው 9 ነጥብ ማሳካት የቻሉት አራቱን ብቻ ነው።

ሁለቱ ቡድኖች የከተማ ተቀናቃኝ ከመሆናቸው ባለፈ በሳምንቱ አጋማሽ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ባደረጉት ጨዋታ ድል ማድረጋቸው የዛሬውን ጨዋታ ተጠባቂ አድርጎታል።

ከዚህ ጨዋታ አስቀድሞ በሌላኛው የሊጉ መርሐ ግብር ቀን 10 ሰዓት ላይ ኮቨንተሪ ሲቲ ከብራይተን ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል።

Exit mobile version