አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሀገሪቱን የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ከእጥፍ በላይ ከማሳደግ ባለፈ የቀጣናውን የኃይል ትስስር እያጠናከረ ነው አሉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ፡፡
ዋና ሥራ አስፈጻሚው እንደገለጹት፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያውያን ጽናት፣ አንድነትና ቁርጠኝነት በተግባር የተገለጠበት ዳግማዊ ዓድዋ ነው፡፡
የግድቡ ግንባታ ኢትዮጵያ በራሷ አቅም የላቀ ስኬት ማስመዝገብ እንደምትችል ለዓለም ያስመሰከረችበት፤ ብሎም አዲስ የታሪክ ምዕራፍ የከፈተ ታላቅ ፕሮጀክት ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ግድቡ ተመርቆ ወደ ሙሉ ሥራ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ የሀገሪቱን የኃይል ማመንጨት አቅም በእጥፍ ከመጨመሩም በላይ፤ ኢትዮጵያ ከዘርፉ የምታገኘውን የውጭ ምንዛሬ ገቢ በእጅጉ ማሳደጉን ገልጸዋል

