አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የ2028 የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር የፍጻሜ ጨዋታ የሚካሄድበት ስታዲየም ይፋ ተደርጓል፡፡
በዚህም የ2028 የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር የፍጻሜ ጨዋታ በአልያንዝ አሬና ስታዲየም እንደሚደረግ የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር አሳውቋል፡፡
አልያንዝ አሬና ለ3ኛ ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታን የሚያስተናግድ ይሆናል፡፡
ከዚህ ቀደም በአልያንዝ አሬና ስታዲየም በፈረንጆቹ 2012 እና 2025 የሻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ መደረጉ ይታወሳል፡፡
በተጨማሪም የ2029 የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር የፍጻሜ ጨዋታ በካምፕ ኑ ስታዲየም እንደሚካሄድ ተመላክቷል፡፡
ካምፕኑ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታን ለሶስተኛ ጊዜ የሚያስተናግድ ይሆናል፡፡
ከዚህ በፊት ካምፕኑ በፈረንጆቹ 1989 እና 1999 የፍጻሜ ጨዋታን ማስተናገዱ አይዘነጋም፡፡
የ2027 የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ በስታዲዮ ሜትሮፖሊታኖ እንደሚካሄድ ይታወቃል፡፡

