አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ተደርጓል፡፡
ትምህርት ሚኒስቴር እንደገለጸው፤ ተማሪዎች የተመደቡበትን ዩኒቨርስቲ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የኦንላይን ሥርዓት በመጠቀም ማየት እንደሚችሉም ጠቁሟል፡፡
የተመደቡበትን ዩኒቨርስቲ ለማየት ይህንን ማስፈንጠሪያ፦ https://student.ethernet.edu.et/view-placement መጠቀም እንደሚችሉም ጠቁሟል፡፡
በምደባው ቅሬታ ያላቸው ተማሪዎች ቅሬታቸውን ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የኦንላይን ሥርዓት ብቻ ይህ ምደባ ይፋ ከሆነበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን መረጃና ማስረጃ በማያያዝ እንዲያቀርቡም አሳስቧል፡፡
የቅሬታ ማቅረቢያ ማስፈንጠሪያ፦ https://student.ethernet.edu.et/complaints
በዚህም በአካል ወደ ትምህርት ሚኒስቴር በመምጣት የሚቀርብ የምደባ ቅሬታ የማይስተናገድ መሆኑን፤ በተጨማሪም የተሳሳተ ማስረጃ ወይም የተጭበረበረ ሰነድ ማቅረብ በፍጹም የተከለከለ መሆኑን ተማሪዎችና ወላጆች እንዲገነዘቡ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

