Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለመጪዎቹ በዓላት የትራንስፖርት እጥረት እንዳይከሰት እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በመስከረም ወር ለሚከበሩ በዓላት የትራንስፖርት ፍሰትን ለማሳለጥ አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ ነው አለ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ።

 

የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ሰንበቶ አባባ እንዳሉት÷ በክልሉ ከመስከረም ወር አዲስ ዓመት መባቻ ጀምሮ የመስቀል በዓልን ጨምሮ የተለያዩ ብሔሮችና ብሔረሰቦች የዘመን መለወጫ በዓላት በደማቅ ሁኔታ ይከበራሉ።

 

በዓላቱን ለማክበር በርካታ እንግዶችና ቱሪስቶች በስፋት ወደ ተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች የሚጓዙ በመሆኑ ከፍተኛ የትራንስፖርት ፍሰት እንደሚኖር አስረድተዋል።

 

የትራንስፖርት ፍሰቱን ለማሳለጥም ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

 

በዓላቱን ምክንያት በማድረግ ሊፈጠር የሚችልን ሰው ሠራሽ የትራንስፖርት እጥረት ለመከላከል ጠንካራ ርምጃ እንደሚወሰድ አቶ ሰንበቶ ገልጸዋል።

 

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር አብርሃም ቲርካሶ በበኩላቸው÷ በቀጣዮቹ በዓላት የትራንስፖርት ፍሰቱን ከማቀላጠፍ ባሻገር የትራፊክ አደጋዎችን ለመከላከል በቅንጅት እንደሚሰራ መግለጻቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።

 

Exit mobile version