Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢጋድ በቀጣናው ሀገራት የማይበገር ኢኮኖሚ መገንባት ቀዳሚ መርሄ ነው አለ

አዲስ አበባ ፤ መስከረም 7፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን (ኢጋድ) በቀጣናው ሀገራት የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ የማይበገር ኢኮኖሚ መገንባት ቀዳሚ መርሁ ነው አሉ ዋና ጸሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር)፡፡

የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን በመቋቋም የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የቀጣናው ሀገራት ወሳኝ የትብብር ማዕከል መሆን እንዳለበት ዋና ጸሐፊው ገልጸዋል።

ኢጋድ በፈረንጆቹ አቆጣጠር እስከ 2035 የሚተገብረውን የቀጣናው የግብርና ምርትና የምግብ ሥርዓት ኢንቨስትመንት ዕቅድ እና የኢጋድ ቀጣና የግብርና ዘር ፖሊሲ የባለሙያዎች ግምገማ አድርጓል።

በዚህ ወቅት ዋና ጸሐፊው በቀጣናው ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችን ለመከላከል በትብብር መቆም የሚያስፈልግበት ወቅት መሆኑን አንስተዋል።

የተቋሙ የ10 ዓመት የግብርና ምርትና የምግብ ሥርዓት ኢንቨስትመንት ዕቅድ በቀጣናው ዘላቂና አይበገሬ የምግብ ሥርዓት መገንባት ያስችላል ብለዋል።

የኢጋድ ቀጣናዊ የግብርና ዘር ፖሊሲም የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን የሚቋቋም ዘላቂ ኢኮኖሚ ማንበር እንደሚያስችል ገልጸዋል።

ዋና ጸኃፊው በአፍሪካ አህጉራዊ ሽግግር ለመፍጠር የኢጋድ ኢኒሼቲቮች ጉልህ አበርክቶ እንዳላቸው ገልጸው ከዚህ ባሻገር የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን በመቋቋም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የቀጣናው ሀገራት በትብብር መሥራት እንዳለባቸውም ማስገንዘባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

Exit mobile version