Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሀገር ሽማግሌዎች እና የሀይማኖት አባቶች ለሰላምና ዕድገት ከፍተኛ ሚና አላቸው – እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የሀገር ሽማግሌዎች እና የሀይማኖት አባቶች ለሁለንተናዊ ሰላምና እድገት ያላቸው ሚና ከፍተኛ ነው አሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)፡፡

የክልሉ የሀገር ሽማግሌዎች የጋራ ፎረም ጠቅላላ ጉባኤ እየተካሄደ ነው፡፡

እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በጉባኤው ላይ እንዳሉት÷ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሀይማኖት አባቶች የተዛቡ አመለካከቶችን በማረም ረገድ ጉልህ ሚና አላቸው።

በተለይም በክልሉ የሚፈጠሩ ግጭቶችን በማብረድ እና አለመግባባቶችን በውይይት በመፍታት ረገድ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሀይማኖት አባቶች ሚናቸውን ሲወጡ እንደነበር አብራርተዋል፡፡

በዚህም የሀገር ሽማግሌዎች እና የሀይማኖት አባቶች በክልሉ ሁለንተናዊ ሰላምና እድገት ላይ ያላቸው አበርክቶ የጎላ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

በጉባኤው የሀገር ሽማግሌዎች የጋራ ፎረም መመስረቻ እና የግንኙነት አሰራር ስርዓት ውስጠ ደንብ ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት እንደሚገኝ የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

Exit mobile version