Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ማንቼስተር ሲቲና ሊቨርፑል ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በ5ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ  መርሐ ግብር ማንቼስተር ሲቲ እና ሊቨርፑል ድል ቀንቷቸዋል፡፡

ቀን 10 ሰዓት ላይ በሜዳው ኢቲሃድ ሰንደርላንድን ያስተናገደው ማንቼሰተር ሲቲ 5 ለ 3 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

አስገራሚ ፉክክር በታየበት የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ አንቶዋን ሴሜኒዮ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር÷  ኤንዞ ፈርናንዴዝ፣ ሪያን ቼርኪ እና ሃላንድ ቀሪዎችን ግቦች ከመረብ አሳርፈዋል፡፡

ሶስቱንም የሰንደርላንድ ግቦች ደግሞ የኔዘርላንድሱ አጥቂ ብሪያን ብሮቤይ በማስቆጠር ሀትሪክ መስራት ችሏል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ ማንቼሰተር ሲቲ ነጥቡን ወደ 15 ከፍ በማድረግ የፕሪሚርሊጉን መሪነት አጠናክሯል፡፡

በሌላ ጨዋታ በውጤት ቀውስ ውስጥ የቆየው ሊቨርፑል ከሜዳው ውጭ ተጉዞ በአሊክሳንደር አይዛክ ግብ ቦርንማውዝን 1 ለ 0 አሸነፏል፡፡

Exit mobile version