Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ታዳሽ ኃይልን ከማመንጨት ባሻገር ሥርጭትና ተደራሽነት ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባል – ፕሬዚዳንት ታዬ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የታዳሽ ኃይል ትኩረቱን ከማመንጨት ወደ ኤሌክትሪክ ተደራሽነትና መሠረተ ልማት ዝርጋታ ሊያሸጋግር ይገባል አሉ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ።

ፕሬዚዳንት ታዬ የኢትዮጵያን ከፍተኛ ልዑክ በመምራት በኒውዮርክ እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም አቀፍ ታዳሽ ኃይል ጉባዔ ላይ እየተሳተፉ ነው።

ፕሬዚዳንቱ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር ዓለም አቀፉ የታዳሽ ኃይል አጀንዳ ኤሌክትሪክ ማመንጨት ላይ ብቻ ከመስራት ይልቅ ኃይሉን ወደ ኢኮኖሚያዊ ሽግግር የሚቀይሩ ሂደቶች ላይ ማተኮር አለበት ብለዋል።

በዚህ መሠረትም መሠረተ ልማቶችን፣ የማስተላለፊያ መስመሮችን እና የኃይል ማከማቻዎችን መደገፍና ማስፋት ያስፈልጋል ነው ያሉት።

የማስተላለፊያ መስመሮች፣ የኃይል ማከማቻዎች እና ጠንካራ የአገልግሎት አሰጣጥ አቅም ሳይኖር ኤሌክትሪክ ማመንጨት ብቻውን ኢኮኖሚያዊ ሽግግር ማምጣት እንደማይችል ጠቅሰዋል።

በመሆኑም ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ድጋፎች ከኃይል ማመንጨት ጀምሮ እስከ ማስተላለፍ፣ ማከማቸት እና ለመጨረሻው ተጠቃሚ እስከ ማድረስ ያለውን ሙሉ የኤሌክትሪክ ሥርዓት ማካተት አለባቸው ብለዋል።

ኢትዮጵያ ካላት 9 ሺህ 761 ሜጋ ዋት የኃይል ማመንጨት አቅም ውስጥ ከ95 በመቶ በላይ የሚሆነው ከታዳሽ የኃይል ምንጮች የሚገኝ መሆኑን አመልክተዋል።

Exit mobile version