Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሚኬል አርቴታ ከአርሰናል ጋር ውሉን ለማደስ ተስማማ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ከእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን ጋር የተሻሻለ አዲስ ውል ለመፈራረም ተስማምቷል።

ስፔናዊው አሰልጣኝ ከአርሰናል ጋር ያለው ኮንትራት በዚህ የውድድር ዘመን መጨረሻ የሚያበቃ ሲሆን ከክለቡ ጋር ስለሚኖረው የወደፊት ቆይታ ላለፉት በርካታ ወራት ድርድር ሲካሄድ ቆይቷል።

አሁን ላይ ታዲያ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ከመድፈኞቹ ጋር የተሻሻለ አዲስ ውል ለመፈራረም የመጨረሻ ስምምነት ላይ መድረሱ ተረጋግጧል።

የአዲሱ ውል ትክክለኛ የጊዜ ርዝመት በይፋ ያልተገለጸ ቢሆንም አርቴታ ከፈረንጆቹ 2019 የጀመረው የስፔናዊው አሰልጣኝ የአርሰናል ቤት ቆይታ ቢያንስ እስከ 10ኛ ዓመቱ ያራዝማል ተብሎ ይጠበቃል።

ከአዲሱ ውል ጋር ተያይዞ የአርቴታ ደመወዝም ከፍተኛ ጭማሪ እንደሚያገኝ የተገለጸ ሲሆን አሁን በዓመት 10 ሚሊየን ፓውንድ የሚያገኘው አሰልጣኙ በአዲሱ ውል እስከ 5 ሚሊዮን ፓውንድ የሚደርስ ተጨማሪ የጉርሻ ክፍያ በማግኘት የዓለማችን ውዱ ተከፋይ አሰልጣኝ ይሆናል ነው የተባለው።

አርቴታ በቅርቡ ስለ ውሉ ድርድር ሲናገር ÷ የአርሰናል ደጋፊዎች ስለ ወደፊቱ መጨነቅ እንደሌለባቸው እና እሱ በአርሰናል ቤት መቆየት እንደሚፈልግ ገልጿል።

አርቴታ በአርሰናል የሚኖረውን ቆይታ ማራዘሙ ክለቡ ከእሱ ጋር የጀመረውን የረጅም ጊዜ ፕሮጀክት ለመቀጠል ያለውን ፍላጎት የሚያሳይ እንደሆነ የዘገበው ቢቢሲ ነው።

በአቤል ነዋይ

Exit mobile version