Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ሜጀር ጄኔራል ገብረ አድሃና ህገ ወጡን የህወሓት ቡድን በመቃወም ወደ ፌዴራል መንግሥት ገቡ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የትግራይ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት የህወሓት ነባር አመራር ሜጀር ጄኔራል ገብረ አድሃና የህወሓትን ከታሪካዊ ጠላቶች ጋር በማበር ሀገር የማፍረስ ተልዕኮና የጦርነት አባዜ በመቃወም ወደ ፌደራል መንግሥት ገብተዋል።
ጄኔራል መኮንኑ በሀገር መከላከያ ሠራዊት ውስጥ በከፍተኛ የአመራር እርከን ላይ ያገለገሉ ሲሆኑ፤ ህወሓት በሀገር ላይ ክህደት እስኪፈጽም ድረስ የመከላከያ መረጃ ዘመቻ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል።
ዕድሜያቸው ለውጊያ ያልደረሱ ህጻናትን ለጦርነት በመማገድ፤ የትግራይ ህዝብን ስቃይ እያበዛ ያለውን የህወሓት እኩይ ስራ በመቃወም ጄኔራሉ ከድርጅቱ መለያየታቸው የህገ ወጡ የህወሓት ቡድን ህልውና ማክተሙን ያሳያል።
Exit mobile version