አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ ከኖርዌይ ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ሚኒስትር ኦስሙንድ ኦክሩስት ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም በሱዳን እና በአፍሪካ ቀንድ ላይ ባሉ ሀገራት የሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ዙሪያ በትኩረት መክረዋል፡፡
በሱዳን ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የሚደረጉ የተቀናጁ ጥረቶችን ለማጠናከር ሃሳብ መለዋወጣቸውንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል፡፡
ውይይቱ በ81ኛው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባዔ መደበኛ ስብሰባ ጎን ለጎን ነው የተካሄደው፡

