አዲስ አበባ፤ መስከረም 15፣2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በመስቀል በዓል ዋዜማ በጉራጌ ዞን 19 መንደሮች የኤሌክትሪክ ሃይል ተጠቃሚ ሆነዋል አለ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፡፡
የመስቀል በዓልን በድምቀት ለማክበር በዝግጅት ላይ በሚገኘው ጉራጌ ዞን ፍትሃዊ የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ በተከናወነ ሠፊ ሥራ በእኖርና እዣ ወረዳዎች የሚገኙ 19 የገጠር መንደሮች ናቸው የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ የሆኑት፡፡
የኤሌክትሪክ መሥመር ዝርጋታውን ለማከናወን ከ132 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገ ሲሆን ÷ በዚህም 2 ሺህ 295 የሚጠጉ ቆጣሪዎች ተገጥመዋል፡፡
ለተከናወነው ሥራ ስኬት 25 ነጥበን 92 ኪ.ሜ መካከለኛ እና 38 ኪ.ሜ ዝቅተኛ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋት መከናወኑን አገልግሎቱ ለፋና ዲጂታል ገልጿል፡፡

