Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመገንባት እንደ ችቦ ተያይዘን የምንነሳበት ወቅት ላይ ነን – ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በትናንት ወረቶች ላይ የዛሬ ስኬቶችን ጨምረን የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመገንባት እንደ ችቦ ተያይዘን የምንነሳበት ወቅት ላይ ነን አሉ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ።

የመስቀል ደመራ ሥነ ሥርዓት በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ በድምቀት እየተካሄደ ነው።

ሚኒስትሯ በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የመስቀል ደመራ የኢትዮጵያ ገጽታ የሚታይበት ድንቅ የአደባባይ በዓል ነው።

የኢትዮጵያ ህብረብሔራዊ አንድነትና አብሮነት በማጠናከር የባህላችንን ድንቅ ውበት የምናንጸባርቅበት፣ ማህበራዊ ትስስር እና ሀገራዊ አንድነት የሚጠናከርበት ታላቅ በዓል ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ብዙ ፈተናዎችን በአይበገርነትና በድል እያለፈች በበርካታ ዘርፎች የልማት ስኬቶችን እያስመዘገበች እንደሆነ ገልጸው፤ ስኬቶቹ የተመዘገቡት በብርቱ ስራ እና በህዝቦቿ የጋራ ጥረትና ትብብር መሆኑን ጠቅሰዋል።

በትናንት ወረቶች ላይ የዛሬ ስኬቶችን ጨምረን የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመገንባት እንደ ችቦ ተያይዘን የምንነሳበት ወቅት ላይ ነን ያሉት ሚኒስትሯ፤ የተጀመረው የስኬት ጉዞ ተጠናክሮ እንዲቀጥል መስራት እንደሚገባ አመልክተዋል።

በትዕግስት ግዛቸው

Exit mobile version