አቶ አብዱልሰላም ዋሪዮ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባዔ ሆነው ተመረጡ Yonas Getnet 2 hours ago አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የጨፌ ኦሮሚያ 7ኛ የሥራ ዘመን የ2019 ዓመት የመጀመሪያ ጉባዔ እየተካሄደ ነው፡፡ ጨፌ ኦሮሚያ እያካሄደ በሚገኘው ጉባዔም አቶ አብዱልሰላም ዋሪዮን የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባዔ አድርጎ መርጧል። በተጨማሪም ወ/ሮ ዘምዘም ሻሎ የጨፌ ኦሮሚያ ምክትል አፈ ጉባዔ ሆነው ተመርጠዋል፡፡