Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኢትዮጵያ እና የካናዳን የቡና ንግድ የሚያጠናክር ዓለም አቀፍ የቡና ኤክስፖ ተከፈተ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ እና ካናዳን የቡና ንግድ የሚያጠናክር ዓለም አቀፍ የቡና ኤክስፖ በቶሮንቶ ከተማ ተከፍቷል፡፡

በኤክስፖው የኢትዮጵያ የቡና ላኪዎች፣ የካናዳ የቡና አስመጪዎችና አቀነባባሪዎች፣ የንግዱ ማህበረሰብ፣ የቡና ምርት ባለሙያዎች፣ ዲፕሎማቶች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

በኤክስፖው መክፈቻ ላይ በካናዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር ቴዎድሮስ ግርማ ÷ በኢትዮጵያ እና በካናዳ መካከል የሚደረገው ቀጥተኛ የቡና ንግድ ካለው የገበያ ፍላጎት እና የምርት አቅም አንፃር ውስንነቶች መኖራቸውን ጠቁመዋል።

ኤክስፖው የኢትዮጵያ ቡና በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ ያለውን ተቀባይነት ከማሳደግ ባሻገር በኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች እና በካናዳ አስመጭዎች መካከል ያለውን ግንኙነት የበለጠ ለማሳደግ ያግዛል ብለዋል፡፡

የካናዳ የቡና ማህበር ተወካይ አና ማንቺኒ በበኩላቸው ÷ ማህበራቸው ከኢትዮጵያ የቡና ላኪዎች ጋር ያለውን ትብብር ለማሳደግ እና አዳዲስ የስራ እድሎችን ለመፍጠር እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡

ኤክስፖው የቢዝነስ ለቢዝነስ ግንኙነትን ለማድረግ እድል መፍጠሩን ገልጸው የኢትዮጵያ የቡና ላኪዎች ከካናዳ አስመጪዎች እና ቡና አቀነባባሪዎች ጋር በቀጥታ እንዲገናኙ አድርጓል ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

Exit mobile version