አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ጀማሉ ጀንበር ( ዶ/ር ) በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ በመሆን ተሹመዋል፡፡
ጀማሉ ጀንበር (ዶ/ር) በከተማ አስተዳደሩ ከ2016 ጀምሮ እስካሁን ድረስ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ ኃላፊነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል።
ቀደም ሲልም የትራንስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ፣የኅብረተሰብ ተሳትፎ እና በጎፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽነር፣ የወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ፣ የሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም የአሽከርካሪ እና ተሽከርካሪ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ በመሆን ማገልገላቸውን የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመለክታል።

