Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት የመንግሥት ምስረታና የ4ኛ ዙር የመክፈቻ ጉባዔ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማ አስተዳደር መንግሥት ምስረታና 4ኛ ዙር የመክፈቻ ጉባዔውን ማካሄድ ጀምሯል፡፡

በጉባዔው በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን ወክለው የተመረጡ የምክር ቤት አባላት ተሳትፈዋል፡፡

ምክር ቤቱ በዛሬው ጉባዔ የምክር ቤቱን አፈ ጉባዔ እና ምክትል አፈ ጉባኤ እንዲሁም የከተማ አስተዳደሩን ከንቲባ እና ምክትል ከንቲባ እንደሚሰይም ተመላክቷል፡፡

በተጨማሪም የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውሳኔዎችን የሚያሳልፍ ሲሆን ÷ የፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሹመትን ጨምሮ የተለያዩ ሹመቶችን እንደሚያጸድቅም ይጠበቃል፡፡

Exit mobile version