Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ለኢትዮጵያ የሰጡት ክብርና ምስጋና

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኬንያ መንግሥትና ሕዝብ ለኢትዮጵያ ትልቅ አክብሮትና ምስጋና አለው አሉ የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ፡፡
ፕሬዚዳንቱ ይህንን የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በተካሄደው የላሙ የነዳጅ ማጣሪያ ግንባታ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ላይ ነው።
ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በመልዕክታቸው ፥ የፕሮጀክቱ ግንባታ ይፋ መሆን አፍሪካ አዲስ ዘመን እየጀመረች እንደሆነ ያወጀ ነው ብለዋል።
በተለይም አፍሪካ በራስ አቅም መገንባት፣ በሀገር ውስጥ ማምረት እና እሴት መጨመር እንደምትችል ያሳየ መሆኑን አመልክተዋል።
በተጨማሪም ፕሮጀክቱ የአፍሪካውያን ትልም በአፍሪካውያን አቅም ፤ አፍሪካዊ ኢንዱስትሪዎችን ለአፍሪካ ብልጽግና መገንባት እንደሚቻል ያረጋገጠ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ኢትዮጵያንና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) በተለየ ሁኔታ ያመሰገኑት ፕሬዘዳንት ሩቶ፥ እኔም ሆንኩ የኬንያ ሕዝብ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከእኛ ጋር ለመሆን ላሳየኸው ቁርጠኝነት ትልቅ አክብሮትና ምስጋና አለን ብለዋል።
ምክንያቱም ይህ አጋርነት ለኬንያ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያና ለቀጣናው ትልቅ ትርጉም ያለው በመሆኑ ነው ሲሉ አውስተዋል።
አፍሪካ ሃብት አላጣችም ፤ እውቀት አላጣችም፤ ገበያም አላጣችም፤ እነዚህን የሚያሰባስብ አቅም ነው መገንባት ያለብን ብለዋል ፕሬዚዳንት ሩቶ በመልዕክታቸው።
በመልካም ፈቃዱ
Exit mobile version