Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች እውቅና ሰጡ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመዲናዋ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እውቅና ሰጥተዋል።
በከተማ አስተዳደሩ በ2018 የትምህርት ዘመን ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የእውቅና መርሐ ግብር ተከናውኗል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፤ በከተማዋ የተመዘገበው ውጤት ጥረት ከተደረገ ውጤታማ መሆን እንደሚቻል ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
በመዲናዋ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች 33 በመቶ የሚሆኑት ጥሩ ውጤት አምጥተዋል ያሉት ከንቲባዋ፤ ይህ ውጤት እንደ ከተማ ከሚፈለገው ውጤት አንጻር ብዙ መስራት እንደሚጠበቅ አመላክተዋል።
ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ዛሬ ተሻላሚ የሆኑ ተማሪዎች ለቀጣይ ዓመታት አቅምና ብርታት እንደሚሆኑ አንስተዋል።
የከተማ አስተዳደሩ ለትምህርት ዘርፉ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሆነ አንስተው፤ በቀጣይ የላቀ ውጤት ለማምጣት መታቀዱን አመላክተዋል።
የሚለገውን ውጤት ለማምጣት በቀጣይ መምህራን፣ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም የተማሪ ወላጆች የበኩላቸውን አስተዋጽኦ አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ነው ያሉት፡፡
በቅድስት ብርሃኑ
Exit mobile version