አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ መስከረም 23 ቀን 2019 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ በሚከበረውን የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል ምክንያት የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ እንደሚሆኑ አስታወቋል፡፡
ነገ መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ሠዓት ጀምሮ እስከ መርሀ ግብሩ ፍፃሜ ድረስ፡-
◉ ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ (22 ወይም ጎላጎል አደባባይ ላይ እና ታች)
◉ ከአድዋ ድልድይ ወደ ዘሪሁን ህንፃ እና ወደ ቅዱስ ዑራኤል አደባባይ (ዘሪሁን ህንፃ መስቀለኛ)
◉ ከአትላስ መብራት ወደ ቅዱስ ዑራኤል አደባባይ (ፒኮክ መብራት)
◉ ከቦሌ ሩዋንዳ ድልድይ ወደ መስቀል አደባባይ (ወሎ ሠፈር አደባባይ ላይ እና ታች)
◉ ከጋዜቦ አደባባይ በደንበል ህንፃ ጀርባ ወደ ፊላሚንጎ እንዲሁም ከጋዜቦ አደባባይ በአዲሱ መንገድ ወደ ለገሃር መብራት (ጋዜቦ አደባባይ)
◉ ከቅዱስ ቂርቆስ ታቦት ማደሪያ ወደ ለገሃር መብራት (ቅዱስ ቂርቆስ ታቦት ማደሪያ መብራት)
◉ ከቀድሞው ብርሃን ኢትዮጵያ መስቀለኛ በአዲሱ መንገድ ወደ ቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን (ብርሃን ኢትዮጵያ መስቀለኛ)
◉ ከአፍሪካ ህብረት ቅዱስ ሚካኤል መስቀለኛ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (አፍሪካ ህብረት ቅዱስ ሚካኤል መስቀለኛ)
◉ ከአፍሪካ ህብረት መብራት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (አፍሪካ ህብረት መብራት)
◉ ከከፍተኛ ፍ/ቤት አደባባይ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ከፍተኛ ፍ/ቤት አደባባይ)
◉ ከሜክሲኮ አረቁ ፋብሪካ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (አረቄ ፋብሪካ መስቀለኛ)
◉ ከሰንጋ ተራ 40/60 ቤቶች መገንጠያ ወደ ሠንጋ ተራ መብራት (ሠንጋ ተራ 40/60 መገንጠያ)
◉ ከጎማ ቁጠባ መብራት ወደ ብሔራዊ ቴአትር (ጎማ ቁጠባ መብራት)
◉ ከሜትሮሎጂ መታጠፊያ ወደ ፖስታ ቤት መብራት (ሜትዮሮሎጂ መታጠፊያ)
◉ ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ኤሚግሬሽን መብራት ( ጥቁር አንበሳ መስቀለኛ)
◉ ከጎላ ቅዱስ ሚካኤል መስቀለኛ ወደ ኤሚግሬሽን መብራት (ጎላ ቅዱስ ሚካኤል መስቀለኛ)
◉ ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ ኤሚግሬሽን መብራት (ቴዎድሮስ አደባባይ)
◉ ከንግድ ማተሚያ መታጠፊያ ወደ ፍል ውሃ መስቀለኛ (ንግድ መታጠፊያ)
◉ ከፓርላማ መብራት ወደ ውጭ ጉዳይ (ፓርላማ መብራት ላይ)
◉ ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ (ሴቶች አደባባይ)
ከረፋዱ 4:00 ሠዓት ጀምሮ የሚዘጋ ሲሆን አሽከርካሪዎች አስቀድመው አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ እያሳሰበ ከንጋቱ 12:00 ሠዓት ጀምሮ በተጠቀሱት መንገዶች ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሽከርካሪ ማቆም የተከለከለ መሆኑን አሳስቧል።
ህብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ሆነ ጥቆማ ለመስጠት በ01-11-11-01-11 እና በ990 ነፃ የስልክ መስመር መጠቀም እንደሚቻል ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

