Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢሬቻ አብሮነትንና ሀገራዊ መግባባትን የሚያጠናክር የጋራ እሴት ነው-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢሬቻ አብሮነትንና ሀገራዊ መግባባትን ከማጠናከር ባለፈ ሀገራዊ ልማትን ለማፋጠን የሚያግዝ የጋራ እሴት ነው አሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፡፡

“ኢሬቻ ”ለሀገራዊ መግባባት” በሚል መሪ ሃሳብ 8ኛው የኢሬቻ ፎረም ዛሬ በአዲስ አበባ ሸራተን ሆቴል እየተካሄደ ነው።

በፎረሙ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ÷ኢሬቻ ምስጋና የሚቀርብበት በዓል ከመሆኑ ባለፈ አንድነትን፣ አብሮነትን፣ መቻቻልንና መከባበርን የሚያጎለብት እሴት ነው ብለዋል።

ኢሬቻ ሰላምን፣ አብሮነትንና መግባባትን ከማጠናከር ባለፈ ዜጎች በጋራ በመቆም ሀገራዊ ልማትን ለማፋጠንና ከድህነት ለመውጣት የሚያግዝ የጋራ እሴት መሆኑን አመልክተዋል።

በአዲስ አበባም የኢሬቻ በዓልን ለማክበር ለሚመጡ እንግዶች መስተንግዶ በማድረግ የበዓሉን እሴት ለማጠናከር ከተማዋ አበክራ  ትስራለች ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል  መስከረም 23 ቀን በአዲስ አበባ ሆራ ፊንፊኔ እንዲሁም በማግስቱ መስከረም 24 ቀን በቢሾፍቱ (ሆራ አርሰዲ) በተለያዩ ደማቅ ስነ-ስርዓቶች ይከበራል።

#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅራዕይ

Exit mobile version