Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ እሴቱን ጠብቆ በድምቀት ተከብሯል – የአዲስ አበባ የተቀናጀ የጸጥታ ግብረ ኃይል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣2019 (ኤፍ ኤም ሲ) “ኢሬቻ ለብሔራዊ መግባባት ” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ከተማ የተከበረው የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል በደመቀና እሴቱን በጠበቀ መንገድ ተከብሯል አለ የአዲስ አበባ የተቀናጀ የፀጥታ ግብረ ኃይል፡፡
በዓሉ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች፣ የውጭ ሀገር ዜጎችና ቱሪስቶች እንዲሁም በርካታ ታዳሚዎች በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል፡፡
በዓሉ ባህላዊ ይዘቱን ጠብቆ በድምቀትና በሰላም እንዲከበር አባገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች፣ ፎሌዎች፣ የመዲናዋ ነዋሪዎች፣ አስተዳደሮች፣ የፀጥታና የደህንነት ተቋማት አመራሮችና አባላት ላደረጉት አስተዋፅኦ የፀጥታ ግብረ ኃይሉ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡
በነገው ዕለትም በቢሾፍቱ የሚከበረው የሆረ አርሰዴ የኢሬቻ በዓል ባህላዊ ይዘቱን ጠብቆ እንዲከበር የፀጥታ ተቋማት ዝግጅታቸውን አጠናቀው ወደ ሥራ መግባታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ ያመለክታል፡፡
Exit mobile version