Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የዓለም የልብ ቀን በጅማ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ማዕከል እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የዓለም የልብ ቀን በጅማ ዩኒቨርሲቲ ሕክምና ማዕከል በነፃ የልብ ምርመራና የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብሮች እየተከበረ ነው።
“አንድም የልብ ምት አታምልጠን” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ በሚገኘው የ2026 የዓለም የልብ ቀን ንግግር ያደረጉት የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ደረጀ እንግዳ (ዶ/ር) ዩኒቨርሲቲው በአካባቢው እየጨመረ የመጣውን የልብ ሕመም ለመከላከልና ለማከም አስፈላጊውን የሰው ኃይልና የሕክምና መሣሪያ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ የልብ ማኅበር ፕሬዚዳንትና ተላላፊ ያልሆኑ ሕመሞች ማኅበራት ህብረት ምክትል የቦርድ ሰብሳቢ እንዳለ ገብሬ በበኩላቸው በ 2018 ዓ.ም በ 45 ቀናት ዉስጥ ብቻ ከ 200 መቶ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የልብ ቀዶ ህክምና መደረጉን ጠቅሰዋል።
በዘንድሮ ዓመትም እስካሁን ለ 60 ዜጎች የልብ ቀዶ ህክምና በማድረግ ተደራሽነቱን ለማስፋፋት እየተሰራ ነዉም ብለዋል።
አክለዉም በጅማ ከተማ የልብ ሕመም ተጠቂዎች ቁጥራቸው ከፍ ያለ በመሆኑ ሕብረተሰቡ ስለ ልብ ሕመም መከላከያና ሕክምና የተሻለ ግንዛቤ ለመፍጠር መርሀግብሩ መዘጋጀቱን አመላክተዋል።
አከባበርሩ በነፃ የልብ ምርመራና የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብሮች የሚቀጥል መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
በአትክልት በቀ
Exit mobile version