Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአዲሱ መንግሥት ምስረታ ሥነ ሥርዓት ዛሬ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲሱ መንግሥት ምሥረታ እና የምክር ቤቱ መክፈቻ ሥነ ሥርዓት በዛሬው ዕለት ይካሄዳል።

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ 42 የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ 10 ሺህ 438 ዕጩዎች እንዲሁም ከ54 ሚሊየን በላይ መራጮች ተሳትፈው በስኬት መጠናቀቁ ይታወሳል።

ጠቅላላ ምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሃዊና ተዓማኒነት ባለው ሁኔታ ነው በስኬት የተከናወነው።

በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 50 ንዑስ አንቀጽ 3 መሠረት የፌዴራሉ መንግሥት ከፍተኛ የሥልጣን አካል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሆኑንና ተጠሪነቱም ለኢትዮጵያ ሕዝብ መሆኑን ይደነግጋል።

የምክር ቤቱ የሥራ ዘመንም በመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ እንደሚጀምር በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 58 ንዑስ አንቀጽ 2 ተደንግጓል፡፡

በተጨማሪም በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 56 መሠረት በምክር ቤቱ አብላጫ መቀመጫ ያገኘ የፖለቲካ ድርጅት ወይም ጣምራ ድርጅቶች የፌዴራሉን መንግሥት የሕግ አስፈጻሚ አካል እንደሚያደራጅና እንደሚመራ ይታወቃል፡፡

በዚህ መሰረትም ዛሬ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም የአዲሱ መንግሥት ምስረታ እና የምክር ቤቱ መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ይካሄዳል።

#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ

Exit mobile version