Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ወ/ሮ አየለች እሸቴ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ ሆነው ተሰየሙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው።

በስብሰባው ወ/ሮ አየለች እሸቴን የምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባዔ አድርጎ በሙሉ ድምጽ ሰይሟል፡፡

ወ/ሮ አየለች እሸቴ ለቀጣይ አምስት ዓመታት የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ ሆነው ለማገልገል በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ

Exit mobile version