አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል።
7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ጉባዔ እየተካሄደ ነው፡፡
ምክር ቤቱ በጉባዔው ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል፡፡
የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አሸናፊ በሆነው ብልጽግና ፓርቲ እጩ ተደርገው የቀረቡት የፓርቲው ፕሬዚዳንት እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡
በመላኩ ገድፍ
#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ

