አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ በድጋሜ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነለው ለተሾሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ ያለዎ መልዕክታቸውን አስተላለፈዋል፡፡
ሊቀ መንበሩ አክለውም፡- ኢትዮጵያ የህብረቱ መቀመጫና የዲፕሎማሲ መዲና በመሆኗ በአፍሪካ ውስጥ ልዩ ስፍራ እንዳላት ገልጸዋል።
በተጨማሪም የአፍሪካን የቅንጅት፣ የሰላም፣ የደህንነትና የልማት አጀንዳዎችን ወደፊት ለማስቀጠል ከጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድና ከመንግስታቸው ጋር በቅርበት እንሰራለን ብዋል፣ የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር፡፡
በእመቤት ሲሳይ

