አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ርዕይ በሚያስብ አእምሮ እና በሚሠሩ እጆች ሲመራ ይሰምራል፣ ይጸናልም አሉ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ።
ፕሬዚዳንቱ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ፥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በድጋሚ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን በመመረጣቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።
ታሪካዊቷን ሀገር ኢትዮጵያን ያገለግሉ ዘንድ የተሳካና ፍሬያማ የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸው መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።

