አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ ዛሬ የመደመር መንግሥት ምሥረታን ስናከብር ፕሬዚዳንቱ ላስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ምስጋናዬን አቀርባለሁ ብለዋል።
ወንድሜን ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎዛን በደስታ ተቀብያለሁ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ አጋርነታችንን ይበልጥ ለማሳደግና በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የወዳጅነት ትስስር እንደምናጠናክር ተስፋ አለኝ ሲሉ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ እና ደቡብ አፍሪካ ለአህጉሩ አንድነት፣ ሰላም፣ ልማትና ብሩህ ተስፋ ባላቸው የጋራ ቁርጠኝነት ላይ የተመሰረተ ጠንካራና ታሪካዊ ግንኙነት አላቸው ነው ያሉት።

