Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሐሙድ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ባስተላለፉት መልዕክት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በድጋሚ በመመረጣቸው ልባዊ ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸው፤ በአዲሱ የሥራ ዘመንዎ ስኬትን እመኛለሁ ብለዋል።

በሶማሊያ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር እንዲሁም ለሕዝቦቻችንና ለአፍሪካ ቀንድ ቀጣና ሰላም፣ መረጋጋትና የጋራ ብልጽግናን ለማስፈን በቅርበት ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡

በእመቤት ሲሳይ

Exit mobile version