Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 7ኛ የስራ ዘመን 1ኛ ዓመት የጋራ መደበኛ ስብሰባ መክፈቻ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦

የታክስ መሰረትን በማዘመን እዳን ወግ ባለው መልኩ ማስተዳደር እንዲሁም የመንግሥት ወጪና ገቢን በአግባቡ የመቆጣጠር አቅም ያድጋል፤
በፌደራል መንግሥትና በክልሎች መካከል ያለው የስራ ቅንጅትና የአፈጻጸም ሁነት የተባበረ፣ የተደጋገፈ፣ ቀልጣፋ እና እንከን አልባ እንዲሆን ይደረጋል፤
የኢትዮጵያን የውጭ ግንኙነት ከተቀባይነት ወደ ተጽእኖ ፈጣሪነት የሚያሸጋግር በተለይም ወዳጆችን በማበርከት የሚተጋ፣ የደመኝነት እይታ ያላቸውን ደግሞ የሚመክር፣ ለሰላምና ለኢኮኖሚያዊ ትስስር ምንጊዜም ቅድሚያ የሚሰጥ ተነሳሽነቶች ያሉትና ዓለም አቀፍ ተቀባይነታችንን የሚያሳድግ ይሆናል፤
በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና አገልግሎት ዘርፍ ከፍ ያለ እመርታ ከምናስመዘግብባቸው ዘርፎች መካከል የሀገራችን የኤሌክትሪክ ተደራሽነት ወደ 65 በመቶ የሚያድግ ይሆናል፤
የውሃ ተጠቃሚነት በስፋት እንዲያድግ ይደረጋል፤
የጤና መድህን ሽፋን ወደ 85 በመቶ ያድጋል፤
የደን ሽፋን አሁን ካለበት 26 በመቶ ከፍ እንዲል ይደረጋል፤
የመሶብ አገልግሎት ማዕከላት ቁጥር እንዲበራከትና ከፍ እንዲል ይደረጋል፤
የተማሪዎች ምገባ ሽፋንም 70 በመቶ እንዲደርስ ይሰራል።
የሀገራችን የፍትህ ዘርፍ የበለጠ እንዲዘምን፤ በሀገራዊ ምክክር የቀረቡ ምክረ ሀሳቦች ወደ ትግበራ እንዲገቡ ይደረጋል።
አስተማማኝ የባሕር በር መሻታችን በጋራ ጥቅም፤ ሰጥቶ በመቀበልና በሰላማዊ መንገድ እውን እንዲሆን ጥረት ይደረጋል፡፡
አጠቃላይ የታክስ ገቢ ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት አንጻር ወደ 9 ነጥብ 26 በመቶ ከፍ እንዲል ይደረጋል፤ የዋጋ ግሽበት ወደ ነጠላ አሀዝ እንዲወርድ አጠቃላይ የታክስ ገቢም ከፍ እንዲል ይደረጋል፡፡
በዓለም መድረክ ኢትዮጵያ ሀላፊነት የተቀበለችው የኮፕ-32 ዝግጅት ሀገራችን ለጉዳዩ ያላትን ከፍ ያለ የሀሳብና የተግባር ተርታ በዓለም ፊት የምታሳይበት በመሆኑ በቁም ነገር ጉዳዮች መሰናዶ ዝግጅት የተዋጣለትና ተጠቃሽ ጉባኤ እንዲሆን ይሰራል፡፡
በመልካም ፈቃዱ
Exit mobile version