Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጠቅላይ ም/ቤቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በመመረጣቸው የተሰማውን ደስታ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመመረጣቸው የተሰማውን ደስታ ገልጿል።

ምክር ቤቱ ባወጣው መግለጫ በ7 ኛው ጠቅላላ ምርጫ ህዝቡ የሰጠውን ውሳኔ ተከተሎ በትላንትናው ዕለት የኢፌዴሪ መንግሥት በመመስረቱ የተሰማውን ደስታ ገልጿል።

የመረጣችሁ ህዝብ እና ሀገራችን ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋትን ሰላም፣ ልማት እና እድገት ለማምጣት በምታደርጉት ጥረት ሁሉ ጠቅላይ ምክር ቤቱ የበኩሉን ድርሻ ይወጣል ሲልም አጽንኦት ሰጥቷል።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ በሀገራችን ወንድማማችነት፣ የህግ የበላይነት እና እኩልነት እንዲሰፍን ከመንግስት እና ከህዝባችን ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ በመግለጫ አመልክቷል።

በኢትዮጵያ ዘመናትን ያስቆጠረው የመቻቻል፣ የመከባበር እና የአብሮነት እሴቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉና ህዝበ ሙስሊሙ እንደ ከዚህ ቀደሙ አዎንታዊ ሚናውን እንዲወጣ አደራ ሲልም አሳስቧል።

#የመደመር_መንግሥት

Exit mobile version