Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የመንግሥት የ2019 ትኩረቶችን አስመልክቶ ያስተላለፉት መልዕክት፦

👉 ሰላም ለኢትዮጵያ ዕድገትና ግስጋሴ ያለውን ዋጋ ያጤነ እና ከመቼውም ጊዜ የበለጠ ህብረትን፣ ትብብርን እና ኢትዮጵያን የሚያስቀድም ተግባር ይከናወናል፤

👉 ጥራትን መሰረት ያደረገ ሁለንተናዊ መዋቅራዊ ሽግግር እንዲኖር ይደረጋል፤

👉 ትምህርት፣ ጤና እና ማህበራዊ ጥበቃን ከስፋት ወደ ጥራት በማሸጋገር ዜጋን ማዕከሉ ያደረገ ልማት ይፋጠናል፤

👉 ለዕድገታችን ቁልፍ ፋይዳ ባላቸው የኢንዱስትሪና የግብርና ግብዓቶች እንዲሁም ዘመናዊ የመሰረተ ልማት ግንባታ አቅማችን እራሱን እንዲችል ይደረጋል፤

👉 የፕሮጀክት እና የፕሮጀክት ፋይናንስ አፈጻጸም ዘመናዊ፣ ፈጣን፣ ቀልጣፋ እና ተጠያቂነት ያለው እንዲሆን ይሰራል፤

👉 የታክስ መሰረትን በማዘመን ዕዳን ወግ ባለው መልኩ ማስተዳደር፤ እንዲሁም የመንግሥት ገቢና ወጪን በአግባቡ የመቆጣጠር አቅም ያድጋል፤

👉 በፌዴራል መንግሥት እና በክልሎች መካከል ያለው የስራ ቅንጅት እና የአፈጻጸም ሁነት የተባበረ፣ የተደጋገፈ፣ ቀልጣፋ እና እንከን አልባ እንዲሆን ይደረጋል፤

👉 የኢትዮጵያን የውጭ ግንኙነት ከተቀባይነት ወደ ተጽዕኖ ፈጣሪነት የሚያሻግር በተለይም ወዳጆችን በማበራከት የሚተጋ፤ የደመኝነት እይታ ያላቸውን ደግሞ የሚመክር፣ ለቀጣናዊ ሰላምና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ምንጊዜም ቅድሚያ የሚሰጥ ተነሳሽነቶች ያሉት እና ዓለም አቀፍ ተቀባይነታችንን የሚያሳድግ ይሆናል፤

#የመደመር_መንግሥት

በትዕግስት ግዛቸው

Exit mobile version